10c. Order

Taxi Amharic

የአጀንዳ ተራ ቁጥር 10c_ትዕዛዝ የስብሰባ
ቀን፦ ፌብሩዋሪ 14፣ 2023
ትዕዛዝ 2023-03

የሲያትል ወደብ ኮሚቴ ትዕዛዝ
በሲያትል-ታኮማ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ እስከ አምስት አመት ለሚሆን ጊዜ በሚያስፈልግበት ጊዜ የሚቀርብ የታክሲ/ የኪራይ
አገልግሎት ክፍያ ፕሮግራም ለማቋቋም።
የቀረበው

ፌብሩዋሪ 14፣ 2023

መግቢያ
የሶስት አመት ለሙከራ የተሰራ ፕሮጀክትን ተከትሎ፣ የሲያትል ወደብ ኮሚቴ ከታክሲ/ የኪራይ አገልግሎት ክፍያ ለሙከራ የተሰራ
ፕሮግራም አንቀሳቃሾች ጋር በጠንካራ ቁጥጥር እና በባለ ድርሻ አካላትን ማግኘት ላይ ተሰማርቷል። የሚከተለው ትዕዛዝ እንደ
ትምህርት እና የቨርቿል ወረፋ አማራጭ መዘርጋት የመሳሰሉ አዳዲስ ነገሮች ጨምሮ የታቀደውን ፕሮግራም መሰረታዊ ነገሮች
ያቀርባል፤ የመንገድ መታጠፊያ ጠርዝ ስራ አስኪያጅ የደንበኛ አገልግሎት ስልጠና ላይ ማተኮር እና ተገዢነትን ማስፈጸም፤ እና
የአሽከርካሪ ስልጠና እና እድገት ፕሮግራሞች ላይ ጥናት ማድረግ።
የትዕዛዙ ጽሁፍ
የወደብ ኮሚቴው በሲያትል-ታኮማ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በሚያስፈልግበት ጊዜ የሚቀርብ የታክሲ/ የኪራይ አገልግሎት
ክፍያ ፕሮግራም የሚከተሉትን መሰረታዊ ነገሮች እንዲያካትት ዋና ዳይሬክተሩን ያዛል።
•
•
•
•
•
•
•

ወደቡ ከአሁኑ በሚያስፈልግበት ጊዜ የሚቀርብ የታክሲ/ የኪራይ አገልግሎት ክፍያ ለሙከራ የተሰራ ፕሮግራም ጋር
በመተባበር የታክሲ ፈቃድ ካላቸው ባለቤቶች ጋር ወደ አዲስ የስራ ስምምነቶች ይገባል፤ የታክሲ ፈቃድ ያላቸው ባለቤቶች
እስከ ማርች 1፣ 2028 ድረስ ይቆያሉ።
በአቪዬሽን ሰራተኞች እንደዚህ አይነት አላማዎች እንዴት እንደሚገለጹ ለአሽከርካሪዎች መመሪያ ለመስጠት፣ የስራ
ስምምነቶችን ማስተላለፍ ህጋዊ ለሆኑ አላማዎች ብቻ የሚፈቀድ ይሆናል።
ወደቡ ከሾፌሩ እስከ SEA በቀጥታ ከሚከፍለው ሁሉን ያካተተ፣ $6/ጉዞ የጉዞ ክፍያ የሚወስድ ይሆናል።
በየትኛውም የቨርቿል ወረፋ አማራጭ ትግበራ የኮሚቴ እርምጃ እንደሚያስፈልግ በመረዳት፣ ወደቡ ከኦፕሬተሮች ጋር
በመገናኘት፣ በትምህርት፣ እና ከአሽከርካሪው ማህበረሰብ ጋር በመመካከር የቨርቿል ወረፋ አማራጮች ላይ ጥናት
ያደርጋል።
ወደቡ ከመንገድ ዳር አስተዳደር ጋር ውል እንዲሁም ክፍያ የሚፈጽም ይሆናል።
ወደቡ በየሩብ አመቱ ባለ ድርሻ አካላትን ማግኘቱን ይቀጥላል።
ወደቡ የታክሲ/ የኪራይ ክፍያ ፕሮግራም ላይ የአሽከርካሪዎችን አስተያየት ለማደራጀት በMotion 2019-03
የተፈቀደለትን የበጎ ፈቃደኛ የአሽከርካሪ ድርጅት እውቅና መስጠቱን የሚቀጥል ይሆናል እንዲሁም ከበጎ ፈቃደኛ
አሽከርካሪዎች ድርጅት ጋር በመደበኛነት መገናኘቱን የሚቀጥል ይሆናል። ወደቡ ፍላጎት ላላቸው አሽከርካሪዎች
የአሽከርካሪ ስልጠና እና የሰው ሃይል እድገት ፕሮግራም ላይ ጥናት ማድረግ እና ማዘጋጀት አለበት።

ትዕዛዝ 2023-03 – በሚያስፈልግበት ጊዜ የሚቀርብ የታክሲ/ የኪራይ አገልግሎት ክፍያ ፕሮግራም ማቋቋም

ገጽ 1 ከ 2

•

•

የወደብ ኮሚቴ የአቪየሽን ኮሚቴ፣ ወይም ተወካዮች፣ ከአሽከርካሪዎች እና ከበጎ ፈቃደኛ አሽከርካሪ ድርጅት ጋር ለማሻሻል
በአይሮፕላን ማረፊያ የመሬት ትራንስፖርት የግጭት አፈታት ስርዐትን መገምገም፣ እና ውጤቶቹን እስከ ኦገስት 30፣
2023 ለኮሚቴው ሪፖርት ማድረግ አለባቸው። እንዲሁም ኮሚቴው፣ ወይም ተወካዩ፣ ለታክሲ/ የኪራይ ክፍያ
ፕሮግራም፣ ወይም ተወካይ የግብይት አማራጮች ላይ ጥናት ማድረግ አለበት።
ወደቡ ይህ ትዕዛዝ በተላለፈ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ደንብን በማክበር ለኮሚቴው ተገዢነትን ለማረጋገጥ እና ሪፖርት
ለማቅረብ ለመንገድ ዳር ስራ አስኪያጁ የውል የደንበኞች አገልግሎት መስፈርቶችን መገምገም እንዲሁም አጽንዖት
መስጠት አለበት።

የታክሲ/ ከSEA ለኪራይ ጉዞዎች ዝቅተኛ ታሪፍ ተቀባይነትን በሚያበረታታው ከሲያትል ወደብ ለኪንግ ካውንቲ ምክር ቤት
በተላከው ደብዳቤ መሰረት፣ በመላው የኪንግ ካውንቲ ለታክሲ/ለኪራይ ጉዞዎች ኪንግ ካውንቲ ያቀረበው የለውጥ ሁኔታን
በተመለከተ ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክሩ ይህ ትዕዛዝ በጸደቀ በ90 ቀናት ውስጥ ለኮሚቴው ሪፖርት ማድረግ ይኖርበታል። በ 2023
መገባደጃ ላይ ኪንግ ካውንቲ አውራጃአቀፍ ዝቅተኛ የታሪፍ መፍትሄ ካላዘጋጀ፣ ኮሚቴው ለታክሲ/በሚያስፈልግበት ጊዜ የሚቀርብ
መንገደኞችን እንዲወስዱ ለተፈቀደላቸው የተቀጠሩ አሽከርካሪዎች ብቻ የሚተገበር አነስተኛ ዋጋ በ SEA ላይ ያስባል።
ትዕዛዙን የሚደግፍ መግለጫ
በስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሩ እና በሰራተኞች ለኮሚቴው እንደቀረበው፣ ጉዳዮች እና ስጋቶች በሚነሱበት ጊዜ ለይቶ ለማቃለል
የታክሲ/የኪራይ ፕሮግራም ትግበራ ከኦፕሬተሮች፣ ከአሽከርካሪዎች፣ እና የታክሲ ፈቃድ ካላቸው ባለቤቶች ጋር ቀጣይነት ያለው፣
ጠንካራ እና በታማኝነት የሚደረጉ ውይይቶችን ያካትታል። የአይሮፕላን ማረፊያ ታክሲ/የኪራይ ፕሮግራም በአሁኑ ጊዜ
ከአሽከርካሪዎች፣ ከኦፕሬተሮች፣ እና ተወካዮች ጋር በበጎ ፈቃደኛ አሽከርካሪ ድርጅት አማካኝነት ቀጣይነት ያለው እና መደበኛ
ውይይት ለማድረግ የተዋቀረ ሂደትን፣ እንዲሁም ወደቡ የመንገድ ዳር አስተዳደር ተቋራጩን እና የግጭት አፈታትን በመቆጣጠር
ረገድ ያለውን ሚና ያጠቃልላል።
የፕሮግራሙ ትግበራ የንግድ መንጃ ፈቃድ (CDL) የሚፈልጉ ፕሮግራሞችን እና ለሌላ የመሬት ትራንፖርት መንገዶችን፣ የጭነት
መኪና ትራንስፖርት፣ ሎጅስቲክስ፣ ወይም ሌላ የቤተሰብ ክፍያ ንግድ እና ከትራንስፖርት ጋር የተያያዙ የሙያ መስኮችን ጨምሮ
ለአሽከርካሪዎች ጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ የሰው ሃይል ልማት ፕሮግራሞችን በመለየት በወደብ ከአሽከርካሪዎች እና ኦፕሬተሮች ጋር
መተባበርን የሚያካትት ይሆናል።
በአፈጻጸሙ ውስጥ የተካተተው ለመንገድ ዳር አስተዳደር አገልግሎቶች የውል መስፈርቶች፣ ለመንገድ ዳር ስራ አስኪያጅ ሰራተኞች
የግጭት አፈታት ወቅታዊ የስልጠና መስፈርቶች፣ እና የመንገድ ዳር አገልግሎቶች ስልጠና እና አስተዳደርን ለማረጋገጥ በቀጣይ ውል
ውስጥ ያለ የስልጠና መስፈርቶች ግምገማ በወደቡ የሚደረግ ግምገማ ነው።

ትዕዛዝ 2023-03 – በሚያስፈልግበት ጊዜ የሚቀርብ የታክሲ/ የኪራይ አገልግሎት ክፍያ ፕሮግራም ማቋቋም

ገጽ 2 ከ 2

Limitations of Translatable Documents

PDF files are created with text and images are placed at an exact position on a page of a fixed size.
Web pages are fluid in nature, and the exact positioning of PDF text creates presentation problems.
PDFs that are full page graphics, or scanned pages are generally unable to be made accessible, In these cases, viewing whatever plain text could be extracted is the only alternative.